sboe

State Board of Education
 

DC Agency Top Menu


-A +A
Bookmark and Share

የቢሮው ታሪክ

የቢሮው ታሪክ

2007 ላይ፣ PERAA (የ “የሕዝብ ትምህርት ሪፍሮም ማሻሻያ አዋጅ 2007 (Public Education Reform Amendment Act of 2007)”) በኮሎምቢያ ዲስትሪክት ውስጥ ልዩ የትምህርት ሪፎርም አድርጓል። የሕዝብ ትምህርት ቤት እንባ ጠባቂ ቢሮ ችግሮችን ለመስማት እና ግጭቶችን ለመፍታት ለወላጆች ዋና ማዕከል በመሆን ተቋቁሟል። አዲሱ የዲሲ የትምህርት ስርዓት በሚተገበርበት ወቅት ግልጽነት እና ተጠያቂነት ለማቅረብ ቢሮው ተዘጋጅቷል።

PERAA ሕግ ለእንባ ጠባቂ ቢሮ (Office of the Ombudsman) የሚከተሉትን ሃላፊነቶችን ሰጥቷል

  • ወላጆች እና ነዋሪዎች ላይ መድረስ፣ እንደ መግባቢያ መሳሪያ ማገልገል፣
  • ቅሬታዎችን እና ስጋቶችን መቀበል፣ ትክክለኛነታቸውን ማረጋገጥ፣ ለቅሬታዎች ምላሽ ማቅረብ፣
  • የስርዓት ችግሮችን መለየት፣ በታዩት አሰራሮች መሰረት ጥቆማዎችን ማቅረብ፣ እና
  • ዓመታዊ ሪፖርት ማቅረብ።

ምንም እንኳን ጠቃሚ ሚና ቢኖረውም፣ ለብዙ ዓመታት ያህል ቢሮው ፈንድ አልቀረበለትም። በ 2012 ላይ፣ የኮሎምቢያ ዲስትሪክት ካውንስል የእንደዚህ ዓይነት ተቋምን ተከታታይ ከፍተኛ አስፈላጊነት እና ጠንካራ የማህበረሰብ ፍላጎት እንዳለ ተገንዝቧል፣ እና በ “ግዛቱ የትምህርት ቦርድ የሠራተኞች ባለስልጣን ማሻሻያ አዋጅ 2012”በኩል በግዛቱ የትምህርት ቦርድ ውስጥ የእንባ ጠባቂን ቢሮ በድጋሚ አቋቁሟል።

በዚህም መሰረት፣ ቢሮው በድጋሚ እንዲቋቋም ተደርጓል እና የሕዝብ ትምህርት ቤት እንባ ጠባቂ ቢሮን በመሾም፣ ፌብውራሪ 26 ቀን፣ 2014 ዓ.ም ላይ ለቤተሰቦች ለኮሎምቢያ ዲስትሪክት ቤተሰቦች ቢሮው በይፋ በሩን ከፍቷል።

2016 ዓ.ም ላይ፣ የቢሮውን መኖር ፈቃድ የሚያሰጠው የመዋቅር አቋም ተሻሽሏል። ይሄ "የግዛቱ የትምህርት ቦርድ ሁሉንም የማሻሻያ አዋጅ 2016" የእንባ ጠባቂውን በጀት እና የሠራተኞችን ስልጣን ሕጋዊ በማድረግ የቢሮውን ችግሮችን ያለአድሎ እና ያለምንም የውጭ ተጽእኖ የመፍታት አቅሙን ያጠናክራል።

የእኛ ሠራተኞች

ለሕዝብ ትምህርት እንባ ጠባቂ

ሴሬና ኤም.ሃይስ ከጃንዋሪ 22 ቀን፣ 2019 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ዓመታት ያህል የጃንዋሪ የሕዝብ ስብሰባ ላይ የእሷ ሚና ላይ ሹመት አግኝታለኝ። ወ/ሮ ሃይስ፣ የዋርድ 5 ነዋሪ፣ ከሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ በሕግ ትምህርት ተማራቂ እና ከዋሽንግተን እና ሊ ዩኒቨርሲቲ በሳይኮሎጂ፣ ሶሺዮሎጂ፣ እና አንትሮፖሎጂ ደግሞ ባችለርስ ዲግሪ ተማራቂ ነች። ወ/ሮ ሃይስ የግጭት አፈታት ስትራቴጂዎች ላይ ግልሰቦችን እና ቡድኖችን አሰልጥናለች እና ቤተሰቦች እራሳቸውን የሚያውቁበትን መንገድ ማሳደግ እና ድምፃቸውን እንዲያገኙ እና እንዲጠቀሙ አበረታታለች። የግጭት አፈታት አስተዳደር ላይ ስልጠኛ ሰጥታለች እና በዲሲ እርስ ቤት ውስጥ በድጋሚ የመግቢያ የሽምግልና አገልግሎቶችን አቅርባለች። ሽምግልና ላይ ላሳየችው ቁርጠኝነት፣ የሽምግልና አቀራረብ ጥራት ተምሳሌትነት በማሳየት፣ እና የሽምግልና ክህሎቶችን የበለጠ ለማሳደግ ባደረገችው ጥረት የ 2017 ሎሪንግ ቻርኩዲያን የዓመቱ ምርጥ በጎፈቃድ አድራጊ (Lorig Charkoudian Volunteer of the Year) ሽልማት አግኝታለኝ። ወ/ሮ ሃይስ የፖሊስ ጠባይን ለመከታተል፣ እና በፖሊስ እና በከተማው ነዋሪዎች መካከል ግንኙነትን ለማሻሻል የሚያገለግሉ መስፈርቶችን ለማውጣት ለባልቲሞር ነዋሪዎች የማዳመጥ ክፍለ ጊዜዎች የተደረጉበት፣ ከፍሬዲ ግሬይ ሞት በኋላ የስምምነት ድንጋጌዎች የወጡበት የትልቅ የቡድን ውይይቶችን አሳልጣለች።

ረዳት የሕዝብ ትምህርት እንባ ጠባቂ

ሪቬል ዲ .ፊቲዝፓትሪክ ኦገስት 2018 ዓ.ም ላይ እንደ ረዳት የሕዝብ ትምህርት እንባ ጠባቂ ተቀጥሯል። በሚሲሲፒ ዴልታ ውስጥ እንደ ተማሪ እና አስተማሪ፣ ለሕዝብ ትምህርት ስርዓት ስኬት ጥቅል ስሜት አካብቷል። በእያንዳንዱ መጀመሪያ፣ ሁለተኛ፣ የምረቃ፣ እና ድህረ ምረቃ ተማሪዎች ደረጃ ላይ ከተማሪዎች ጋር ሰርቷል። ከእንባ ጠባቂን ቢሮ ከመቀላቀሉ በፊት፣ ሪቪል ከአንድ ዓመት በላይ የተማሪ ተሟጋች ቢሮ (Office of the Student Advocate) ውስጥ እንደ ተባባሪ ሰርቷል። እንደዚሁም ከ American Civil Liberties Union፣ Mississippi Center for Justice፣ እና Amara Legal Center ጋር ሰርቷል። ሪቬል ከሚሲሲፒ ግዛት ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቢ.ኤስ ዲግሪ እና ከሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ ህግ ትምህርት ጄ.ዲ አግኝቷል።

ረዳት እንባ ጠባቂ

ቤሪል ትራውዝ- ጁርማን በቢሮው ውስጥ 2015 እና 2016 እንደ ተባባሪ ከሰራ በኋላ ፌብውራሪ 2017 ላይ እንደ ረዳት እንባ ጠባቂ ተቀጥሯል። ከወጣቶች ጋር ያለፉት አስር ዓመታትን አሳልፏል እና በትምህርት ስርዓት ውስጥ ያላቸውን መብቶች ወላጆች እና ልጆች እንዲረዱ መርዳት ያስደስተዋል። ቤሪል ሽምግልና፣ ማሳለጥ፣ እና የግጭት አሰለጣጠን ላይ ስልጠና ወስዷል እና የእንባ ጠባቂውን ቢሮ የሚመጡ ወላጆች እና ቤተሰቦችን ለማበረታታት እነዚህን ክህሎቶች እጠቀማለሁኝ ብሎ ያስባል። ቤሪል ቢኤ እና ማስተርስ ዲግሪውን ከጆርጅ ማሰን ዩኒቨርሲቲ፣ የእርስበኣርስ እና አነስተኛ ቡድን ግጭት አፈታት ዘዴዎች ላይ በማተኮር ከስኩል ኦፍ ኮንፍሊክት አናሊስስ ኤንድ ሪዞሊሽን ተቀብሏል።

የፕሮግራም ረዳት

(ክፍት ቦታ) .